የኢትዮጵያ አየር መንገድ የAPEX የመንገደኞች ምርጫ ሽልማትን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የAPEX የመንገደኞች ምርጫ ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተጓዦች የላቀ የመዝናኛ እና የገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት በማቅረብ የዘንድሮውን የAPEX የመንገደኞች ምርጫ ሽልማትን አሸነፈ፡፡
አየር መንገዱ በዓመታዊው የAPEX የመንገደኞች ምርጫ ውድድር ላይ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ (Best Entertainment Award in Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ገመድ ዓልባ ኢንተርኔት አገልግሎት (Best Wi-Fi Award in Africa) ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል፡፡
በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ የሆነው Airline Passenger Experience Association (APEX)፤ የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ በየዓመቱ ለአየር መንገዶች ዕውቅና እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል፡፡