ቀጥታ፡

በአሌ ዞን ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የኮላንጎ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተመርቆ ለአገልግሎት ተዘጋጀ

ጂንካ፤ ሰኔ 13/2016 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሌ ዞን ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የኮላንጎ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተመርቆ ለአገልግሎት ተዘጋጀ።

ኮሌጁን ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደና የክልሉ ካብኔ አባላት ናቸው።

የኮሌጁ ዲን አቶ ናቸው ኦሎ ለኮሌጁ ግንባታ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ተናግረዋል። 

የኮሌጁ ግንባታ ሥራ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁን ገልጸው፤ ኮሌጁ መማሪያ ክፍሎች፣ ሰርቶ መሳያ፣ ቤተ-መጻህፍትና የስብሰባ አዳራሽ አካተው የያዙ ስድስት ሕንጻዎች እንዳሉት ተናግረዋል።


 

አቶ ጥላሁን ከበደና የካቢኔ አባላቱ ኮሌጁን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን፣ በቀጣይ ኮሌጁን በግብአትና በሰው ሀይል ለማሟላት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኮሌጁ መገንባት በአካባቢው የሰለጡኑ፣ አምራችና ሥራ ፈጣሪ ብቁ ተማሪዎችን ለማፍራት ያግዛል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ጥላሁን ለኮላንጎ የመጀመሪያ ሆስፒታል ግንባታም ዛሬ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም