ቀጥታ፡

በ28ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ይከናወናሉ

አዲስ አበባ፤ሰኔ 13/2016(ኢዜአ)፦በ28ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋሉ።

ሻሻመኔ ከተማ እና ፋሲል ከተማ ከቀኑ በ9 ሰዓት ሲጫወቱ፤ በሐዋሳ ከተማና በወልቂጤ ከተማ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ደግሞ ምሽት 12 ሰዓት ይከናወናል።

በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የሚመራው ሻሸመኔ ከተማ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች በአንዱ አቻ ሲወጣ በአራቱ ተሸንፏል።

አራት ጎሎችን ሲያስቆጥር አሥር ጎሎች ተቆጥረውበት በ14 ነጥብ 15ተኛ ደረጃን በመያዝ  ወራጅ ቀጠና ላይ ተቀምጧል።

ሻሸመኔ ከተማ ከፋሲል ከተማ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ጨምሮ፤ በቀጣይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀምበሪቾን የሚገጥም ሲሆን፤ በሊጉ ለመቆየት ከራሱ ውጤት ባለፈ የወልቂጤ ከተማን ነጥብ መጣል ይጠብቃል ።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ፋሲል ከተማ በበኩሉ፤ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች በሁለት አሸንፎ፣ በሁለት የተሸነፈ ሲሆን በአንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ ወጥቷል። 

ሦስት ጎሎችን ሲያስቆጥር፤ በአንፃሩ ሦስት ጎሎችን በማስተናገድ በ40 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

በ28ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ምሽት 12 ሰዓት ጨዋታ በሐዋሳ ከተማና በወልቂጤ ከተማ መካከል ይደረጋል።

ሐዋሳ ከተማ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለት አሸንፎ፣ ሁለት ተሸንፎና አንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ ወጥቷል።

ሰባት ጎሎችን ሲያስቆጥር፣11 ጎሎች ደግሞ ተቆጥረውበት በ36 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ወልቂጤ ከተማ ደግሞ ካለፉት አምስት ጨዋታች አምስቱንም በመሸነፍ የወራጅ ቀጠና ስጋት ውስጥ ገብቷል።

ባለፉት አምስት ጨዋታዎች 2 ጎል ሲያስቆጥር 13 ጎሎች ተቆጥረውበት በ16 ነጥብ 14ተኛ ደረጃን ይዟል።

ሐዋሳ ከተማና ወልቂጤ ከተማ ከዚህ ቀደም 7 ጊዜ ተገናኝተው፤ ሐዋሳ ከተማ አራት ጊዜ ሲያሸንፍ፤ ወልቂጤ ከተማ ደግሞ አንድ ጊዜ አሸንፏል፤ በቀሪዎቹ 2 ጨዋተዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

በእነዚህ ጨዋታዎች ሐዋሳ ከተማ 10 ጎሎችን ሲያስቆጥር፤ ወልቂጤ ከተማ 7 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

28ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  እስከ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ ም ድረስ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም