ቀጥታ፡

የተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ይሰራል - ዶክተር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የተመዘገበው ኢኮኖሚያዊ እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎችን መስራት ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን ተግባር ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)ገለጹ።

የመንግስት የ2016 ዓ.ም የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ከአገልግሎቱ ሰራተኞች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት እድገቱን ለማስቀጠል እየተተገበሩ ያሉ ኢንሼቲቮች በከፍተኛ ሁኔታ ማደግ አለባቸው፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት የውስጥና የውጭ ጫናዎችን ተቋቁመን ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ችለናል - አቶ አሕመድ ሽዴ

እድገቱ በሁሉም ዘርፍ ቀጣይነትእንዲኖረው በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ለኢኮኖሚ እድገቱ ሰላም ወሳኝ በመሆኑ መንግስት የጀመረውን ሰላምን የማረጋገጥ ሥራ በሁሉም አካባቢዎች በተሻለና በተጠናከረ ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የ10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸምን በተመለከተ ገለጻ ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ የፈረንጆቹ 2023-2024 የዓለም አማካይ የኢኮኖሚ እድገት 3 ነጥብ 2 በመቶ መሆኑን አንስተዋል።


 

ኢትዮጵያ በተጠቀሰው ጊዜ 7 ነጥብ 9 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧን ገልጸው በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአፍሪካ 5ኛ ከዓለም ደግሞ 57ኛ ግዙፉ ኢኮኖሚ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣዩ ዓመት የሀገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚ በ8 ነጥብ 3 በመቶ እንዲያድግ ይሰራልም ብለዋል፡፡

በሁሉም ዘርፎች የተመዘገበው እድገት ኢትዮጵያ በለውጥ ምህዋር ውስጥ መሆኗን ማሳያ ነው - ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

በዚህም ግብርናው 6 ነጥብ 1 በመቶ፣ ኢንዱስትሪው 2 ነጥብ 8 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፉ 7 ነጥብ 1 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ መናገራቸውን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዋጋ ግሽበቱን አሁን ካለበት 25 ነጥብ 5 በመቶ ወደ 12 በመቶ ለማውረድ እንደሚሰራ ሚኒስትር ዴኤታዋ አስረድተዋል።

ይህንን ውጤት ለማምጣትም በሥራ ፈጠራ ላይ በትኩረት ለመስራት መታቀዱን በመግለፅ በውጭ ሃገር የስራ ስምሪት 700 ሺህ ዜጎች እንዲሁም በሃገር ውስጥ ለ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም