ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተጀመረ  

አዲስ አበባ፤ሰኔ 12/2016 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል።

የኢዜአ ሪፖርተር በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተዘዋወረባቸው ትምህርት ቤቶች ፈተናው በተረጋጋ መልኩ በጥሩ ዝግጅት መጀመሩን አረጋግጧል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አይዳ አወል፤ በእሸቴ የቅድመ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ፈተናውን አስጀምረዋል።

ለፈተናው በተቀናጀ ዝግጅት የመፈተኛ ጣቢያዎችን ምቹ የማድረግ ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ተማሪዎች በተረጋጋና ምቹ በሆነ ሁኔታ ፈተናውን ጀምረዋል ብለዋል።

በአዲስ አበባ የስድስተኛ ክፍለ ከተማ አቀፍ ፈተና  ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

በመዲናዋ በ183 የመፈተኛ ጣቢያዎች 86 ሺህ 222 ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱም ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም