ቀጥታ፡

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ካሜሩን አቀና

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 12/2016 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ካሜሮን ዱዋላ አቀና።

የኢትዮጵያ ልዑክ ዛሬ ጠዋት ወደ ካሜሮን ዱዋላ ከተማ መጓዙን፤ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ሽኝት እንዳደረጉለትም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም