ቀጥታ፡

1ሺህ 445ኛው ኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9/2016(ኢዜአ)፦ በመላው ሀገሪቱ የተከበረው 1ሺህ 445 ኛው ኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

በዓሉ ሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ለመላው የሀገሪቱ ሕዝብ እንዲሁም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይም ለሀይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ለወጣቶች ግብረ-ኃይሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

የፀጥታ ኃይሎችም ከህብረተሰቡና ከበዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር በመቀናጀት የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ በመወጣታቸው ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም