ቀጥታ፡

የዓባይ ቀጣናዊ ውህደትና ምክንያታዊ አጠቃቀም ዓመታዊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 8/2016(ኢዜአ)፦ ሶስተኛው  የዓባይ ቀጣናዊ ውህደትና ምክንያታዊ አጠቃቀም ዓመታዊ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የምክክር መድረኩም "የጋራ ሀብት ለጋራ የወደፊት የተሻለ እጣ ፋንታ፤ የዓባይ ፍትሕዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም ለትብብር እና ቀጣናዊ ውህደት" የሚል መሪ ሃሳብ ተሰጥቶታል።

በመድረኩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር  አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)፣ የተለያዩ አገራትን የወከሉ አምባሳደሮች  የተለያዩ አገራት የውሀ ሀብት የስራ ኃላፊዎች፣ ምሁራንና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ የዓባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ያለፉት14 ዓመታት የውሃ አስተዳደር፣ የውሃ ኃይል አማራጭ ለቀጣናዊ ውህደትና ትብብር እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖና የዓባይ ተፋሰስ የተጽዕኖ የቅነሳ ስትራቴጂክ ስልቶችን የሚዳስሱ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ምክክር እየተካሄደባቸው ይገኛል።

የምክክር መድረኩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም