ቀጥታ፡

ዶክተር ዓለሙ ስሜ በጅቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ የገቢ-ወጪ ሂደቱን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ሰኔ 06/2016 (ኢዜአ)፦ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ ዛሬ በጅቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ ተገኝተው አጠቃላይ የገቢ-ወጪ ሂደቱን ጎበኝተዋል።

ይህ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና የሚወጡ አጠቃላይ ምርቶች የሚስተናገዱበት ሲሆን፣ በተለይም የአፈር ማዳበሪያን አስመልክቶ ወደ ሃገር ቤት የሚደረገው ዝውውር እንዲጠናከር ሁለት አዳዲስ የማዳበሪያ ከረጢት መስፊያ ማሽኖች ወደ ኦፕሬሽን እንዲገቡ ሚኒስትሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በጉብኝቱም ላይ ከሚኒስትሩ ጋር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን ጨምሮ የወደብ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና በጅቡቲ የኢትዮጵያ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም