40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ሰኔ 30 ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ሰኔ 30 ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2016(ኢዜአ)፦ ሰኔ 16 ቀን 2016 ሊካሄድ የነበረው 40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ወደ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም መራዘሙን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
በተመሳሳይ ከሰኔ 11 እስከ 15 ቀን 2016 ሊካሄድ የነበረው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሰኔ 25 እስከ 29 ቀን እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ ገልጿል፡፡
ውድድሮቹ የሚካሄዱት በሐዋሳ ከተማ መሆኑንም ፌዴሬሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡