ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ድንገተኛ ህልፈት የተሰማትን ሀዘን ገለጸች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2016(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳውሌስ ካሉስ ቺሊማና ሌሎች ዘጠኝ ተሳፋሪዎች ድንገተኛ የአውሮፕላን አደጋ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን ገለጸች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሀዘን መግለጫ ለማቾቹ ቤተሰቦች፣ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለማላዊ ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝቷል።

በዚህ የሀዘን ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከማላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና ሕዝብ ጎን መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም