በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሰብሳቢነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን አፈፃፀም በጥልቀት በመመልከት ማካሄድ ጀምሯል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4 /2016 (ኢዜአ)፡- በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሰብሳቢነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን አፈፃፀም በጥልቀት በመመልከት ማካሄድ ጀምሯል።

ከግምገማ መድረኩ በተጓዳኝ ከ2010 እስከ 2015 ዓመተ ምህረት የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መፅሃፍ ይፋ ሆኗል ብሏል።

ይህ መፅሃፍ በተጠቀሰው ዘመን የተላለፉ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በዝርዝር እንደሚያመላክት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።


 

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል የሚያከናውነው የመሰነድ ተግባር አንዱ የሆነው ይህ መፅሃፍ ለታሪክ ስነዳ እና መረጃውን ለሚሹ ሁሉ ጠቃሚ የሆነ የሰነድ ዝግጅት ስራ አካል መሆኑም ተጠቅሷል።

ዛሬ ይፋ የሆነው መፅሃፍ ውስን ቅጂዎች ለፌደራል እና ለክልል ተቋማት የሚሰራጩ ሲሆን መረጃውን ለሚፈልጉ ሁሉ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረገጽ ላይ የሚጫን መሆኑም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም