የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀናት ግምገማ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2016(ኢዜአ)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀናት ግምገማ ጀመረ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት የዘንድሮው የበጀት አመት ከመጠናቀቁ በፊት የመጨረሻ የሆነውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀናት ግምገማ ጀምረናል ብለዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደሁልጊዜው የየሴክተሮችን አፈፃፀም እንገመግማለን ሲሉም ገልጸዋል።

ክፍተቶችን እናጤናለን፤ በጥንካሬዎች ላይ ለቀጣይ ስራዎች እንነሳለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም