ቀጥታ፡

ከተማ አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2016 (ኢዜአ)፡- ከተማ አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ መሰጠት ተጀመረ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቅኝት ባደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ያለ ምንም ችግር በተረጋጋ  መንፈስ  ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑን መገንዘብ ችሏል፡፡ 

ለአብነትም በየካ ክፍለ ከተማ  በ15 የፈተና  ጣቢያዎች ተማሪዎች ፈተናቸውን  መውሰድ  ጀምረዋል፡፡   


 

የየካ ክፍለ ከተማ  ዋና ስራ አስፈጻሚ  አቶ ብርሃኑ ረታ የካ ምስራቅ ጮራ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት  በመገኘት  ፈተናውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የፈተናው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱ በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።

በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና በ182 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ86 ሺ 672 ተማሪዎች እንደሚሰጥ ከትምህርት ቢሮው የተገኘው ያመለክታል ።

ከተማ አቀፍ ፈተናው ዛሬ እና ነገ የሚሰጥ ይሆናል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም