አቶ አሕመድ ሽዴ ከኳታር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ  ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2016(ኢዜአ)፦ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ከኳታር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅትም አቶ አሕመድ ሽዴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከን መልዕክት ለኳታሩ አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ አስረክበዋል፡፡


 

መልዕክቱ የኢትዮጵያ እና የኳታርን ታሪካዊ ወዳጅነትና የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚችሉባቸውን መንገዶች ላይ ያተኮረ  መሆኑን ከዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም