ቀጥታ፡

ክልሎች የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን ተቀናጅተን ብናለማ ሀገራችንን በአጭር ጊዜ እንቀይራለን - ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ

አሶሳ ፤ ሰኔ 3/2016(ኢዜአ)፦ ክልሎች የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን የበለጠ ተቀናጅተን ብናለማ የሃገራችንን የድህነት ታሪክ በአጭር ጊዜ መቀየር እንችላለን ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ተናገሩ::

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ዛሬ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።


 

በመድረኩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በወቅቱ እንዳሉት አፋርን ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሀብቶች አሏቸው።

አንዳችን ያለንን ለሌላው በማካፈልና ተቀናጅተን ብናለማ ከድህነት በአጭር ጊዜ መውጣት እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ በመላው ኢትዮጵያውያን ርብርብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋነኛ ማሳያ ነው ሲሉም በውይይቱ ለተሳተፉ የክልሉ ነዋሪዎች ለአብነት ጠቅሰዋል።

ድህነትን በመጸየፍ በመደጋገፍ እና በቁርጠኝነት በመነሳት ውጤት በማምጣት ፀጋችንን በሚገባ ካለማን በቅርቡ ያደጉ ሃገራት  ከደረሱበት ከመድረስ የሚገታን ጉዳይ የለም ሲሉም አቶ አወል ተናግረዋል።

"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሃገራዊ ክብር እና ሉዓላዊነት"  በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ውይይት ተሳታፊዎችም ሀሳብ እና አስተያየቸውን እየሰጡ ነው።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም