ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ጋር ነጥብ ተጋርታለች

አዲስ አበባ፤ሰኔ 2/2016(ኢዜአ)፦በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አራተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች።

በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ማምሻውን በተደረገው ጨዋታ ጋብርኤል ዳድዚ በ29ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ጅቡቲን መሪ አድርጎ ነበር።

ይሁንና የመቻል አጥቂ ብዙም ሳይቆይ በ30ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች።

ውጤቱን ተከትሎ በምድብ 1 የምትገኘው ኢትዮጵያ በ3 ነጥብ በነበረችበት 5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን በማጣሪያው የመጀመሪያ ነጥቧን ያገኘችው ጅቡቲ የመጨረሻውን 6ኛ ደረጃ ይዛለች።

ዋልያዎቹ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጊኒ ቢሳው ባደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በምድብ 1 የምድቡ መሪ ግብጽ ከጊኒ ቢሳው እንዲሁም ቡርኪናፋሶ ከሴራሊዮን ነገ በተመሳሳይ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም