የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሠልጠኛ ማዕከል ለአዲስ ሰልጣኞች የስልጠና መክፈቻ ስነ-ስርዓት አከናወነ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2/2016 (ኢዜአ)፦ የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማሠልጠኛ ማዕከል ለአዲስ ሰልጣኞች የስልጠና መክፈቻ ስነ-ስርዓት አከናውኗል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በፈቃደኝነትና በሞራል ሀገራቸውን በውትድርና ሙያ ለማገልገል የመጡ ወጣቶችን የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና በመስጠትና በማብቃት የተቋሙን የሰው ሃይል ለማጠናከር ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መምጣቱን ተናግረዋል።

ሰልጣኞችም በስልጠና ቆይታቸው የሚገጥሟቸውን ውጣ ውረዶች በጥንካሬ በማለፍ ጠንካራ ጓዳዊ ዝምድናን በማጎልበት ለሀገር መከታ መሆን እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል።


 

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አበባው ሰይድ ሰልጣኞች አርዓያ ሆነው በመሠልጠንና ጥንካሬን ሙያዊ ብቃትንና የአዕምሮ ብስለትን በመፍጠር ከውስጥና ከውጭ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ትንኮሳዎችን በመመከት ዘመናዊ ሠራዊት የመገንባቱ ሂደት መደገፍ እንዳለባቸው፤ ብቁ ሆነው ሥለጠናውን ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የማሠልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ ሠልጣኞች በማሰልጠኛ ቆይታቸው የሚሰጣቸውን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመሰልጠን፣ በስልጠናው ሂደት የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በቆራጥነት ማለፍና በጠንካራ ወታደራዊ ዲስፕሊን ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም