ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው የአፍሪካ ሃገራት 5ኛ ሆነች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መካከል በአምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የአለም የገንዘብ ድርጅት(IMF) ገለጸ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መካከል አምስተኛ ደረጃን የያዘችው በሃገር ውስጥ ጠቅላላ ገቢዋ (GDP) 205 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በማስመዝገብ ነው

በዚህም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አምስተኛ ከዓለም ደግሞ በ57ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ደቡብ አፍሪካ ፣ግብፅ፣አልጄሪያ እና ናይጄሪያ ደግሞ በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ከአንድ እስከ አራተኛ ደረጃን የያዙ ሀገራት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም