ቀጥታ፡

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነት ክብር" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

ድሬደዋ፤ ሰኔ 2/2016 (ኢዜአ)፦ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነት ክብር" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በድቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ የሚመራ ህዝባዊ ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ " ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነት " በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው ።

በውይይቱ ላይ የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር እንደተናገሩት፤  እንደ አገር ያሉንን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ሃብቶች በመጠቀም ከድህነትና ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል።

እነዚህን ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ  ሌት ተቀን መረባረብ ይገባልም ብለዋል።

በተለይም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በየዘርፉ የተጀመሩትን ጥረቶች ይበልጥ በማሳደግ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንደሚገባ ነው የገለፁት።

በውይይቱ ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ ህብረተሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም