ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2016 (ኢዜአ)፡ ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በአሸናፊ ከበደ የክዋኔ ጥበባት ማዕከል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመታደሜ ደስ ብሎኛል ብለዋል።
አሸናፊ ከበደ ከያኒ ብቻ ሳይሆን የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር ነበር።
የአዲሱ ማዕከል ዳይሬክተር ግርማ ይፍራሸዋ ደግሞ በቀደመው እና በአሁኑ የኢትዮጵያ ሙዚቃ መካከል ድልድይ በመሆን ያገለግላል።
ይህን መሰል ድልድይነት እና ቀጣይነት በሁሉም ተቋሞቻችን አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ሙዚቃ ኃይል እንዳለው ገልጸው፤ ይህን ኃይል ለወጣቶቻችን አብርሆት ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጥበባት መጪውን ትውልድ ቅርጽ በማስያዝ እና የከተማችንን የቱሪዝም መስሕብ በማላቅ ከፍ ያለ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው፤ ይህን ዐቅም በምሉዕነት መጠቀም ይገባናል ብለዋል።