የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ከSES ሲንየር ማኔጅመንት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ከSES ሲንየር ማኔጅመንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 30/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ከSES የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት ሲንየር ማኔጅመንት ጋር ተወያይተዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በሉግዘምበርግ በሚገኘው የካምፓኒው ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው አገልግሎቱን በቀጣይነት በጥራት በሚሰጥበት እና በባለሥልጣኑ የሪጉላቶሪ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል ።
በውይይቱም በSES በኩል የአገልግሎት ጥራት እና ቀጣይነትን ወደፊት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑንና በአሁኑ ጌዜ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የሳተላይት የአገልግሎት ጊዜው ሲጠናቀቅ ያለምንም የአገልግሎት መቆራረጥ ለመተካት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ካምፓኒው አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው በባለሥልጣኑ ህጋዊ እውቅና ላላቸው መገናኛ ብዙኃን መሆኑንና በቀጣይም በዚሁ መንገድ ብቻ የሚያስተናግድ መሆኑን በውይይቱ ወቅት አሳውቋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው በካምፓኒው በኩል ባለሥልጣኑ ተልዕኮውን እንዲወጣ እየተደረገ ላለው የስራ ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ካምፓኒው ከደንበኞቹ ጋር ፊት ለፊት የሚያደርገውን ውይይት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ለሀገር የኮርፓሬት ማህበራዊ ኃላፊነት መገለጫ የሚሆኑ ስራዎችን እንዲሰራ መጠየቃቸውን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።