ቀጥታ፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 30/2016(ኢዜአ)፦ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ ሁሉን ዓቀፍ የጤና አገልግሎትን ለማረጋገጥ እና በቀጣይም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤን ለማጠናከር ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር እንደምትሰራ የጤና ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ድርጅቱ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፉ በሰው ኃይል እና በፋይናንሲንግ እንዲጠናከር፣ የክትባት ተደራሽነት እንዲሰፋ እንዲሁም የወባ እና የኮሌራ በሽታ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ድጋፉን እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ የዓለም የጤና ደንብ ማሻሻያዎች ውስጥ ላሳየችው የነቃ ተሳትፎ አድናቆታቸውን መግለጻቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም