"አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
"አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው
ድሬዳዋ ፤ግንቦት 30/2016 (ኢዜአ)፡- "አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ ኢዜአ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ፣በድሬዳዋ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት ተጠሪ ኢብራሂም የሱፍ፤ ፣ የፌዴራልና የድሬዳዋ አስተዳደር አመራር አባላት፣ የአየር ንብረት ለውጥና አረንጓዴ ልማት ላይ በማተኮር የሚሰሩ ተቋማት ተወካዮች፣ የዘርፉ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።
ፓናሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎችና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ዘላቂ የልማት ግቦች፣ በአረንጓዴ ልማት የኢትዮጵያ ተሞክሮ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በሚመለከት የመገናኛ ብዙሃን ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
የፓናል ውይይቱ እንደ አገር እየተሰሩ ያሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ዘላቂ ብልፅግናን ከማረጋገጥ አንፃር ባላቸው ፋይዳ ዙርያ የጋራ አረዳድ እንዲኖር ለማስቻል ያለመ ነው።
በዚህም በህዝቦች የነቃ ተሳትፎ የተጀመሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል አበርክቶው የጎላ እንደሚሆን ተገልጿል።