"አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ነገ በድሬዳዋ አስተዳደር ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
"አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ነገ በድሬዳዋ አስተዳደር ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29/2016(ኢዜአ)፦ "አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ ኢዜአ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት ነገ በድሬዳዋ አስተዳደር ይካሄዳል።
በመድረኩ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ያተኮሩ የውይይት መነሻ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
ፓናሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ዘላቂ የልማት ግቦች፣ በአረንጓዴ ልማት የኢትዮጵያ ተሞክሮ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በሚመለከት የመገናኛ ብዙሃን ሚና በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚያተኩር ተገልጿል።
በመድረኩ የፌዴራልና የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የአየር ንብረት ለውጥና አረንጓዴ ልማት ላይ በማተኮር የሚሰሩ ተቋማት ተወካዮች፣ የዘርፉ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ።