ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት አደረጉ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስያ ጉብኝታቸው ማምሻውን በመመለስ የሶስት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁት የሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በቤቶች ልማት በቱሪዝም እና በግብርና በተለይም በሀገር ውስጥ የማዳበሪያ ምርት ላይ ያተኮረ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ሰባ ዘጠኝ ኢንቨስተሮችን ያካተተው ከፍተኛ ልዑክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን በህዳር ወር በሳዑዲ - አፍሪካ ጉባኤ ወቅት ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ የተከናወነ ነው።