በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎትን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተሰራ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎትን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተሰራ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎትን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
በስብሰባው የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከንቲባዎች፣ ሚኒስትሮች እና የተቋማት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚህ ወቅት፥ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አስተዳደርን እና ሀገራዊ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን አዲስ ፖሊሲ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።
አደጋን በራስ የመሸከም አቅም ማዳበር ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅድመ አደጋ፣ በአደጋ እና በድህረ አደጋ የሚሰሩ ስራዎች በታቀደው መሰረት በተናበበ መልኩ መፈፀም እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።
እንደሀገር አደጋን በራስ አቅም መቋቋም እንችላለን የሚለውን ትልቅ አብዮት ለማሳካት አስቻይ ሁኔታዎች እንዳሉም ነው የተናገሩት።
ለአብነትም ከለውጡ ወዲህ በአረንጓዴ አሻራ በስንዴ ልማት በሩዝና በሌሎችም መስኮች የመጡ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ ጠቁመዋል።
ከተረጅነት ለመላቀቅና እርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን የባህል ለውጥ እንደሚያስፈልግና ልመናን መፀየፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።