ቀጥታ፡

በጀነራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የመከላከያ ሠራዊት 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ታደመ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29/2016(ኢዜአ)፦ በመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የመከላከያ ሠራዊት 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ታደመ፡፡


 

ክብረ-በዓሉ የጅቡቲ የመከላከያ ሚኒስትር ሀሰን ኦመር መሃመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት አታሼዎች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች መከበሩን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም