በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሳተፉ አካላት እነማን ናቸው?

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄደው የአጀንዳ ልየታ ምክክር ምዕራፍ የሚከተሉት አካላት ተሳትፈዋል።

እነሱም፦

👉121 የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች

👉228 የተቋማት እና የማህበራት ተወካዮች

👉52 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች

👉128 የመንግስት አካላት ተወካዮች

👉100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች

👉16 የፓለቲካ ፓርቲዎች

👉11 ሞደሬተሮች (ውይይቶቹን በማስተባበር) ተሳትፈዋል።

እነዚህ ባለድርሻ አካላት በቡድን የተወያዩባቸውን አጀንዳዎች ግንቦት 26/2016 ዓ.ም ለተወካዮቻቸው ሰጥተዋል፡፡

በሂደቱ ሁሉም ተወካዮች በሞደሬተሮች አጋዥነት አጀንዳዎችን አደራጅተዋል፡፡

ግንቦት 27/ 2016 ዓ.ም የአምስቱ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ ማቅረባቸውንም የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም