በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በሳዑዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በሳዑዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በሳዑዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ሥምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈረመ።
ሥምምነቱ የተፈረመው ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮ-ሳዑዲ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ነው።
ሥምምነቱን የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል አይናለም አባይነህ (ዶ/ር) እና የሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሁሴን ሙጂብ ፈርመውታል።
ሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የተመራው 79 አባላትን የያዘ የሳዑዲ አረቢያ የኢንቨስትመንትና የንግድ ልዑካን ቡድን ትላንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል።