የባለድርሻ አካላት ወኪሎች አጀንዳዎችን እያደራጁ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የባለድርሻ አካላት ወኪሎች አጀንዳዎችን እያደራጁ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2016(ኢዜአ)፦ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች አጀንዳዎችን እያደራጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ።
ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያስተባበረ የሚገኘው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ ለሰባተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው።
የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች፣ ሦስቱ የመንግሥት አካላት ተወካዮች፣ የማኅበራት እና ተቋማት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች በአምሥት ቡድኖች ተከፍለው ላለፉት ቀናት አጀንዳዎቻቸውን አስመዝግበዋል።
ከአምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ ተወካዮች ደግሞ ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን እያደራጁ ይገኛሉ ብሏል።
ከሰዓት በኋላ በሚኖረው ክፍለ ጊዜ ደግሞ የተደራጁት አጀንዳዎች ለጉባኤው ይቀርቡና ምክክር ይደረግባቸዋል፡፡
በዚህ ምክክር የሚደራጁት አጀንዳዎች የአዲስ አበባ ከተማ የምክክር ምዕራፍ ውጤት እንደሚሆኑ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።