ጃፓን የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ስራ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች - ኢዜአ አማርኛ
ጃፓን የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ስራ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2016 (ኢዜአ)፦ የጃፓን መንግሥት ኢትዮጵያ ለምታከናውነው የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና መልሶ ማቋቋም ተግባር የሚውል 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች፡፡
ገንዘቡ ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተጣቂዎችን ዲሞቢላይዝ የማድረግ፣ ስልጠናንና የአቅም ግንባታን ለማጎልበት ለሚያድርገው ጥረት እንደሚውል ተመላክቷል።
የድጋፍ ስምምነቱ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የብሄራዊ ተሀድሶ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዬ ይህደጎ በተገኙበት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እና የተመድ የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ጂ ዶ መካከል መፈረሙን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በሀገሪቱ በስምንት ክልሎች የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መልሶ መቋቋምና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ሰላማዊ ህይወት እንዲመሩ የማድረግ ስራን ይሰራል።