የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋርድስ መክፈቻ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋርድስ መክፈቻ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2016(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋርድስ መክፈቻ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዓለም አቀፉ ስታርትአፕ አዋርድስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኪም ባል እና የተለያዩ ስታርትአፕ ተወካዮች ተገኝተዋል።
መርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ ስታርትአፕ አዋርድስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ተባባሪ አዘጋጅ ነው።
የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋርድስ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይቆያል።
በመርኃ ግብሩ የተለያዩ ስታርትአፖች ተወዳድረው ለአሸናፊዎቹ ሽልማት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
በዛሬው መርኃ ግብር ኢትዮጵያን ወክለው በምስራቅ አፍሪካ የግሎባል ስታርትአፕ አዋርድስ የሚሳተፉ ስታርትአፖች ይፋ ይሆናሉ።