ቀጥታ፡

ባለድርሻዎችን ወክለው በምክክሩ እየተሳተፉ የሚገኙ አካላት

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የምክክር ምዕራፍ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ተሳታፊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የትኞቹን አካላት ወክለው እየተሳፉ ይገኛሉ?

1. የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች

👉ከየወረዳው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወክሉ የተመረጡ ተወካዮች

2. የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች

👉በአዲስ አበባ ከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች

3. የተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ)

👉የሃይማኖት ተቋማት

👉ሲቪል ማህበራት

👉የአሰሪዎች ማህበራት

👉የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን

👉የመምህራን ማህበር

👉የአካል ጉዳተኞች ማህበራት

👉የሙያ ማህበራት

👉የቀድማው ሰራዊት ማህበር(ተቀናሽ ሰራዊት ማህበር)

👉የጋዜጠኞች ማህበር

👉የዩኒቨርሲቲ መምህራን (የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት)

👉የንግድ ማህበራት ምክር ቤት

👉የሴቶች እና ወጣቶች ማህበራት

4. የመንግስት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ)

👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት

👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች

👉የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች

👉የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን

5. ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች

👉በተለያዩ ዘርፎች በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው፣ አንቱታን ያተረፉ እና ተፅዕኖን መፍጠር የሚችሉ ግለሰቦች

ኢትዮጵያ እየመከረች!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም