ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዓለም አቀፍ ኦዲት መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዓለም አቀፍ ኦዲት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።  

ዓለም አቀፍ ኦዲቱ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስተባባሪነት በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ትብብር ለመጀመሪያ ጊዜ ከዛሬ ግንቦት 26 እስከ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል። 

በማስጀመሪያ መርኃ-ግብሩ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ሲሳይ ቶላ፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ዘርፍ ዳይሬክተር አስራት ቀጀላ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴንጌ ቦሩ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግሥቴ፤ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች እና የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ኦዲተሮችን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም