ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል ለአደረጉላቸው አቀባበል አመሰገኑ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል ለአደረጉላቸው አቀባበል አመሰገኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል ለአደረጉልን አቀባበል አመሰግናለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ ትስስር ከስድሳ አመታት በላይ ያስቆጠረ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የመጪው ጊዜ ግንኙነታችንም የበለጠ ጠንካራ እና ዘርፈ ብዙ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ የፀና ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም