ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ሃውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ሃውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25/2016 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ሃውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮርያ ቹንቺዮን ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ሃውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው የኢትዮጵያ የኮርያ ጦርነት ዘማቾች መታሰቢያ መዐከልንም ጎብኝተዋል።
ይህ መታሰቢያ ከደቡብ ኮሪያ እና ከተባበሩት መንግሥታት ኃይሎች ጋር መስዋዕትነት የከፈለው እና አስተዋፅዖ ያበረከተው የኢትዮጵያ ቃኘው ሻለቃ በክብር የሚታወስበት ሲሆን የኢትዮጵያን እና የደቡብ ኮሪያን ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር የተሰራ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።