የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሴራሊዮን ፍሪታውን ከተማ በረራ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሴራሊዮን ፍሪታውን ከተማ በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 23/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ምዕራባዊቷ የአፍሪካ አገር ሴራሊዮን ፍሪታውን ከተማ በረራ ጀመረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ መዳረሻውን በየጊዜው እያሰፋ ነው።
በተለይም ደግሞ አየር መንገዱ የፓን አፍሪካን እሳቤ በማንገብ የአፍሪካ አገራትን እርስ በርስ ለማስተሳሰር እየተጋ መሆኑን ነው የገለጹት።
በዛሬው እለትም በረራ የጀመረባት ፍሪታውን ከተማ አየር መንገዱ በአፍሪካ 64ተኛ መዳረሻው መሆኗን ጠቁመዋል።
ዛሬ ወደ ሴራሊዮን የተጀመረው ይህ በረራ በሳምንት 3 ጊዜ የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉት 147 በላይ አውሮፕላኖች 136 ዓለም አቀፍና 22 የአገር ውስጥ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል።