የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሰኔ 30 ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሰኔ 30 ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ግንቦት 22/2016 (ኢዜእ):-ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ የሚያደርጉት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ጨዋታው የሚካሄድበት ስታዲየም በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ኢዜአ ከፌዴሬሽኑ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ ቡና ሃዋሳ ከተማን እንዲሁም ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ መድንን በግማሽ ፍጻሜው በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፋቸው ይታወቃል።
የውድድሩ አሸናፊ ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።