አለም አቀፍ የሀረር ቀንን በተሳካ መልኩ ለማክበር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - አቶ ጌቱ ወዬሳ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22/2016(ኢዜአ)፦26ኛውን አለም አቀፍ የሀረር ቀን በተሳካ መልኩ ለማክበር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ።

ከ26ኛው አለም አቀፍ ቀን በዓል ጋር በተያያዘ ከክልሉ አጠቃላይ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንዳሉት 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን የተሳካ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ከበዓሉ ጋር በተያያዘም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መረባረብ ይገባልም ብለዋል።


 

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን በስኬት እንዲጠናቀቅ አመራሩ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበው የበዓሉ መከበር ገጽታ በመገንባት የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጎለብት ከማድረግ አንፃር መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር አስረድተዋል።

አለም አቀፍ የሀረር ቀን ኩነቶች በስኬት እንዲከበሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ቀን 35 ቀናት የቀሩት መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም