ሁለተኛው የቀይ ባሕር ቀጣና ጂኦ-ፖለቲካል ለውጥና የባሕር ደኅንነት ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22/2016(ኢዜአ)፦  ሁለተኛው የቀይ ባሕር ቀጣና ጂኦ-ፖለቲካል ለውጥና የባሕር ደኅንነት ላይ ያተኮረ  ውይይት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። 

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት መኮንኖች፣ በኢትዮጵያ የተወከሉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ምሁራንና ሌሎች ተሳታፊ አካላት ተገኝተዋል። 


 

በምክክር መድረኩ ላይ በቀይ ባሕር ቀጣና የሚስተዋለው የሰላምና ደኅንነት ሥጋት፤ በመርከብ አገልግሎት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖና በፍትሃዊ የወደብ አገልግሎት የዓለም አቀፍ ልምድና ተሞክሮን የሚዳስሱ የውይይት መነሻ ጽሁፎች ቀርበው ምክክር እየተካሄደባቸው ይገኛል። 

በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በተዘጋጀው መድረክ ላይ በቀይ ባሕር ቀጣና አዳዲስ የደኅንነት ሥጋቶችን፣ ፍትኃዊ የወደብ አጠቃቀምና የዓለም አቀፍ ልምድና ተሞክሮ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ አመላካች ኃሳቦች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም