የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 29ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2016(ኢዜአ)፦ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው፤ የማዕድን ሚኒስቴርን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን እንደሚያደምጥ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት ጋር ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ያደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የሚቀርቡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን እንደገና የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ እና የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን ለመደንገግ የሚቀርብን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራም እንዲሁ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም