በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2016 (ኢዜአ)፡- በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
በጉባኤው ላይ ከአቶ አህመድ ሺዴ በተጨማሪ በኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
ጉባኤው "የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን እና ዓለም አቀፍ የፋይናንሺያል አርክቴክቸር ማሻሻያ" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ እንደሚገኝ በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡