የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከኒውዝላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2016(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከኒውዝላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊኒስተን ፒተር ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች እንዲሁም በሰብዓዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።

በተጨማሪም የጋራ ፍላጎትን መሰረት ባደረጉ የሁለትዮሽ፣ አህጉራዊና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም