የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሌዥ ከተማ ከቀዳሚ የጭነት አየር መንገዶች ተርታ ተሰለፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሌዥ ከተማ ከቀዳሚ የጭነት አየር መንገዶች ተርታ ተሰለፈ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት በቤልጂየም ሌዥ ከተማ ቀዳሚ ከሆኑ የጭነት አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉን አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ በፈረንጆቹ 2023 ከ160 ሺህ ቶን በላይ ጭነት ከሌዥ ከተማ ወደ ተለያዩ አህጉራት በብቃት ማመላለሱን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም መሠረት ወደ አፍሪካ፣ ኤስያ፣ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሀገራት በትጋት በማመላለስ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑም በመረጃው ተመላክቷል፡፡