ቀጥታ፡

የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21 /2016(ኢዜአ)፡-የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን የሥራ እንቅስቃሴ ዛሬ ጎብኝተዋል።

የሕዝብና የንግድ መገናኛ ብዙኃን የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ተቋማዊ የሥራ እንቅስቃሴና የለውጥ እርምጃዎችን ጎብኝተዋል። 


 

በባለሥልጣኑ የሥራ ክፍሎች ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን የክትትል፣ ድጋፍ፣ ቁጥጥርና አስተዳደር እንዲሁም ተቋማዊ የሥራ እንቅስቃሴና የለውጥ እርምጃዎችን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ እና ሌሎች የባለሥልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች አስጎብኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም