በምክክር ሂደቱ ለሀገር የሚበጁ ሃሳቦችን በማንሳት የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተናል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 21/2016(ኢዜአ)፦ በምክክር ሂደቱ  ለሀገር የሚበጁ ሃሳቦችን በማንሳት የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ተሳታፊዎች ተናገሩ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በተጀመረው አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ መርሃ ግብር የሚሳተፉ የማህበረሰብ ክፎሎች በተዘጋጀው ቦታ ተሰባስበዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ከተገኙት መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች በምክክር ሂደቱ ለሀገር የሚበጁ ሃሳቦችን በማንሳት የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

በመድረኩ የመምህራን፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮች በምክክር መርሀ ግብሩ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው የምክክር ምዕራፍ ከ2 ሺህ 500 በላይ ተወካዮች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በምክክር ምዕራፍ መርሃ ግብሩ ሶስት ዋና ዋና ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን እነሱም ተሳታፊዎች በምክክርና በውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን ማምጣት፣ አጀንዳዎቻቸውን የጋራ በማድረግ ያሰባስባሉ፣ ያደራጃሉ እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳቦችን ያንሸራሽራሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም