በድጎማ በጀትና በክልል መንግስታት የጋራ ፎረም ላይ የሚመክር ጉባኤ ነገ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል

ሀዋሳ፤ ግንቦት 20/2016(ኢዜአ)፡- በፌደሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀት እና በክልል መንግስታት የጋራ ፎረም ላይ የሚመክር ጉባኤ በነገው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

በመድረኩ ላይ ለመሳተፍም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገርን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ዛሬ ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የመወያያ ጹሑፎች ቀርበው ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም