ለአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በወላይታ ሶዶ ከተማ አቀባበል እየተደረገለት ነው

ሶዶ ፤ ግንቦት 20/2016 (ኢዜአ)፡-የአርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቀላቀሉን ተከትሎ በወላይታ ሶዶ ከተማ ደማቅ አቀባበል እየተደረገለት ነው።

በአቀባበል መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ሥራ ኃላፊዎች፣ የዞንና ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ደስታ እየገለጹ ነው። 

የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2016 ዓ.ም የውድድር ዘመንን በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀሉ ይታወሳል።

ቡድኑ በ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ በተጨማሪ ክልሉን ወክሎ የሚሳተፍ ሁለተኛው ክለብ ይሆናል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም