ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በ77ኛው የዓለም የጤና ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በ77ኛው የዓለም ጤና ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው።

የዓለም ጤና ጉባኤ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

“ሁሉም ለጤና፣ ጤና ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ ላይ ከ190 በላይ አባል ሀገራት ተወካዮችና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በጉባዔው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በተለያዩ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳዎች ላይ የሚመክረው ጉባዔው እስከ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ  ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም